- በዛሬው እለት በደብረታቦር ከተማ አተዳደር የስማርት ሲቲ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በዶ/ር ዮሴፍ የመጀመሪያውን ሶፍትዌር ስለጠና እና የከተማውን ዌይብሳይት(website) ትውውቅ ተካሂዷል፡፡ በስልጠና መርሃግብሩ የኮሚቴው አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃብታሙ ጌታሁን ኮሚቴውን በማስተባባር በቨርችዋል ሚቲንግ(virtual meeting) በደ/ር ዮሴፍ የሚሰጠውን ስልጠና በጋራና በተናጥል ስልጠናውን እንዲከታተሉ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የቀረቡ ዋና ዋና ነጥቦች የዌይብሳይት ምንነት እና ጠቀሜታ፤ ስማረት ሲቲ ሲታሰብ ያለዌይብሳይት ተሻጋሪ እንደ ማይሆን፤ ዌይብሳይቱ ከሌሎች ሶፍትዌሮች ጋር በጋራ አቀናጅቶ አንደሚሰራ እና ሌሎች ጨምሮ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በከተማችን ውስጥ እብዛም በሶፈትዌር የሰለጠነ የሰው ሃይል ባለመኖሩ የመረጃ አያያዛችን ደካማ እንደሆነና ለከተማችን የእድገት ማነቆ፤ የከተማው ኑአሪ ለአገልግሎት ሲመጡ እንደሆነባቸው ተገልጧል፡፡ የከተማውን ዌይብሳይቱት ለመመስረት እና ስልጠና ለመስጠት ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ ቢሆንም ወንድማችን ዶ/ር ዮሴፍ ለሃገርና ለወገን በቆርቆር ጊዜውን ሳይሰስት በነፃ ዌይብሳይቱን በመመስረት እና የመጀመሪየውን ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከተማችን ወደላቀ የእድገት ደረጃ ለማሻገር ወንድማችን ዶ/ር ዮሴፍ አብረውን እንደሚዘልቁ ቃል ገብተውልናል፡፡ እኛም አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በክቡር ከንቲባ የተጣለብን አደራ ለመወጣት በአግባቡ ጊዜአችን ተጠቅመን በሚገባ ሰልጥነን እና ሌሎችን በማሰልጠን ወደ ተግባር በመቀየር የደብረታቦርን ከተማ ስማርት ሲቲ ማድረግ ግዴታችን መወጣት እንዳለብን በጋራ ተግባብትን እንደምንሰራ ቃል ገብተናል፡፡ ክብር ከንቲባችን አይተነው፤ ሰምተነው፤ አለያም ደግሞ አስበነው የማናውቀውን የስማርት ሲቲ ምስረታ ስላስጀመሩልን ከልብ እያመሰግን እኛም በበኩላችን ከወንድማችን ደ/ር ዮሴፍ ጋር በመሆን የሁለታችሁንም ዕራይ እንደምናሳካው አንጠራጠርም፡፡
‹‹እናመሰግናለን››
‹‹ስማርት ሲቲ የከተማችን ታሪክ መታጠፊያ የከፍታ ማማ ነው››